የገቢዎች ሚንስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታክስ ኦዲት ብር 15 ቢሊዮን 502 ሚሊዮን 37 ሺህ 22 ብር የተወሰነ ሲሆን አፈፃፀሙ 115.11 በመቶ ነው ተብሏል፡፡
የታክስ ኦዲቱ በሁሉም የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተከናወነ ነው፡፡
ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብር 12 ቢሊዮን 278 ሚሊዮን 415 ሺህ 275 ብር ሲሆን መካከለኛ ግብር ከፋዮች ጽ/ቤት ደግሞ 1 ቢሊዮን 367 ሚሊዮን 407 ሺህ 362 ብር ከታክስ ኦዲት እንደተወሰነ ታውቋል፡፡
ምስራቅ አዲስ አበባ ብር 440 ሚሊዮን 900 ሺህ ፍሬ ግብር የኦዲት ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን ቀሪው በሌሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወሰነ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ 3481 ፋይሎችን ኦዲት ለማድረግ አቅዶ 3193 ፋይሎች ኦዲት አደርጓል፡፡
በሔኖክ አስራት
ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም











