ልጁን በመስሪያ ቢሮው ስም የሰየመው ኢንዶኔዢያዊ አነጋጋሪ ሆኗል

ሳሜት ዋህዩዲ ይባላል ስራውንና ስራ ቦታውን በጣም ከመውደዱ የተነሳ የስራ ክፍሉን ስም ወስዶ የልጁ መጠርያ አድርጎታል፡፡

በአሁን ሰአት የዚህ የ 5 ወር ህፃን ልጅ ስምና አባቱ የሚሰራበት የስራ ክፍል ስም ተመሳሳይ የሆነ ሲሆን ፤ስታትስቲካዊ መረጃዎች ተግባቦት ቢሮ፤ ተብለው ይጠራሉ፡፡

ገና ከማግባቱ በፊት ነው ሳሜት ልጅ ስወልድ ልጄን በስራ ክፍሌ ስም ነው የምጠራው ሲል ለራሱን ቃል የገባው፤ ገና ከመጋባታቸውም በፊት ነበር ይሄንን ጉዳይ ለእጮኛው ግልፅ ያደረገላት፡፡ እሷም ሁኔታውን ተገንዝባ ያመነችበት!

የመጀመርያ ልጃቸው ሴት ስለነበረች ለእሷ የተለመደ አይነት ስም ነው ሊሰጣት የፈለገው፤ ባለፈው አመት ታህሳስ ወር ላይ ሁለተኛ ልጃቸው ወንድ ሲሆን ግን ስሙ ማን ተብሎ እንደሚጠራ ወሰነ ፤ ፤ስታትስቲካዊ መረጃዎች ተግባቦት ቢሮ፤ (Statistical Information Communication Office)
የኢንዶኔዢያ ሚዲያ እንደዘገበው ለሳሜት ስራ ቦታው ሁለተኛ ቤቱ ነበር፡፡

ልጁ ሲያድግ ስሙን ማስታወቅ አስቸጋሪ እንደሚሆንበት ግን ግልፅ እንደሚሆን በማሰብ ወላጆቹ ካሁኑ ዲንኮ ሲሉ ቅፅል ስም አውጥተውለታል፡፡

ልጁ ሲያድግ ስሙ ደስ ባይለውስ ተብሎ ይህ ስራውን ወዳድ ኢንዶኔዢያዊ ሲጠየቅ ይለምደዋል ሲል በአጭሩ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሚስት ይሄን የስም አወጣጥ ብትቀበለውም የሷ ቤተሰቦች ግን ተቃውመው ነበር፤ ባልና ሚስት ከመጋባታቸው በፊ የገቡት ውል እንደሆነ ሲሰሙ ግን ትተውታል፡፡

ለሁላችንም የምንወደውን ስራና የስራ ቦታ ይስጠን!

በሔኖክ አስራት
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *