ራማፎሳ ኤኤንሲ (ANC) ሙስናን ለማስቆም አለመቻሉን አምነዋል

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ አገዛዝ ወቅት ገዥው ፓርቲ ሙስናን ለመከላከል አለመቻሉን አምነዋል፡፡

ዙማ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት በሙስና የተጠረጠሩ ክሶችን ለመመርመርና ፍትህ ለማሰጠት በቂ ስራ አልሰራም ብለዋል፡፡

ኤ.ኤን.ሲ ተጠያቂነትን ለማስፈፀም የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ የሚጠብቀውን ያህል እንዳልሰራ በመግለጽ ሙስና የህግ የበላይነት እንዳይረጋገጥ አድርጓል ብለዋል፡፡

“ስልጣንን እና የመንግስትን ሀብቶችን ያለአግባብ መጠቀምን ለመከላከል ፓርቲው የጎላ ጥረት ማድረግ እንደነበረበት ሁላችንም እናውቃለን” ብለዋል ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ነው የዘገበው፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዙማ በዘጠኝ ዓመቱ የሥልጣን ዘመናቸው ማጭበርበር ፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ከአስር በላይ ከሙስና ጋር የተያያዙ ክሶች ተመስርቱባቸዋል ፡፡

እርሳቸው ግን ይህንን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *