ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የቤት ስጦታ ተበረከተላቸው።

በካራማራ ጦርነት የዚያድባሬን ታንኮች በእጅ ቦንብ እንዳጋዩ የሚነገርላቸው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት እንደሰጣቸው ተሰምቷል።

በዛሬው ዕለትም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የቀበሌ ቤት እንደተሰጣቸው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ተናግረዋል።

አሊ በርኪ ጐታ ኦሮሞ›› [አሊ በርኪ የኦሮሞ ጀግና] የተሰኘ የሻለቃ ባሻ አሊ በርኬን ህይወት የሚያስቃኝ መጽሐፍ ተጽፎላቸዋል።

መፅሃፉ በ1969 እና 1970 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በተደረገው ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ የፈጸሙትን ታሪክ የሚዳስስ ነው፡፡

በአንድ ወቅት በሀገሪቱ ከሚታተሙ ጋዜጣ ጋር ባደረጉተ ቃለ ምልልስ “ጡረታዬ አልተከበረልኝም ጡረታዬ ቢከበርልኝ በእዚህ እድሜዬ ኩንታል እሸከም ነበር? አገሬ ለከፈልኩት ውለታ ፊት ነስታኛለች ጡረታ እኮ የለኝም” ብለው ነበር።

በዛሬው ዕለትም የከተማ አስተዳደሩ ከ15 አመታቸው ጀምሮ ለሀገራቸው ነጻነት ለተዋደቁት የክብር ኒሻን ተሸላሚው ጀግና ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የቤት ስጦታ ማበርከቱን ከአዲስ አበባ ፕርስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በትላንትናው ዕለትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 134 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች ሰጥተዋል።

በከተማዋ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን እና የሁሉንም የከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *