ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ37.4 ሚሊየን ብር በላይ በሽያጭ ከተወገዱ ንብረቶች ገቢ መገኘቱን የፌደራል ንብረት ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም አስታወቀ

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ40 መ/ቤቶች 94 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ፤ 30 ሚሊዮን 204 ሺ ብር በላይ ማስወጉን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የ25 መስሪያ ቤቶችን 360 ሎት ያገለገሉ ንብረቶችና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ አልሙኒየምና ስቲል ፣ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በመሸጥ 7 ሚሊዮን 252 ሺ ብር በላይ የተገኘ ሲሆን በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ንብረቶች 37 ሚሊዮን 456 ሺ 525 ብር በላይ ገቢ መገኘቱን መስሪያ ቤቱ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም አሳውቋል፡፡

በተያያዘም ባለፈው ዘጠኝ ወራት 548 ሚሊየን ብር ውል መፈረሙ የተገለፀ ሲሆን፤ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በውል አስተዳደር በኩል ከ17 አቅራቢ ድርጅቶች ጋር 19 ውሎችን መፈራረሙን የገለፀ ሲሆን ፤ በጠቅላላው 548 ,077 ,038 ብር ውል ተፈርሞ 187 ባለበጀት መስሪያ ቤቶችንና 22 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏልም ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *