ኦፌኮ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ሁሉንም አቀፍ ያልሆነ ምርጫ ከማካሄድ መጣደፉን አቁመው የዕርቅና ብሔራዊ መግባባት መድረክ እንዲያመቻቹ ጥሪ አቀረበ፡፡የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)ፖርቲ ከብሔራዊ መግባባት መሸሽ ያገራችንን ችግሮች እያባባሰና እያወሳሰበ ነው በሚል ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷ፡፡

ኦፌኮ እንዳለው የአገሪቱ ውስብስብ ችግሮች በብሔራዊ መግባባት ይፈቱ ዘንድ ያደረጋቸው እጅግ ብዛት ያላቸው ጥሪዎች እየተደብሰብሰ በመታለፉቸው፤ አገራችን ሊትወጣ ከማትችልበት ሁለንትናዊ መመሰቃቀል ውስጥ ገብታለች፡፡

በበኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብን ያፈናቀለ፣ ሕይወትን ያጠፋና ንብረትን ያወደመ ግጭት ተፈጥሯል፡፡
በኦሮምያ ክልል በወለጋና ጉጂ ዞኖች እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች ግጭት በመስፋፋቱ ብዙ ሕይወት እየጠፋ ነው፡፡

ትግራይ ውስጥ ያለው አጠቃላይ ቀውስ ከኛ አልፎ የዓለም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እነዚህና ሌሎች ችግሮች እያሉ መንግስት በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበና በኛ እምነት ችግሮችን ያባብስ እንደሆነ እንጂ፤ ችግሮችን የማይፈታ ምርጫ እንዲካሄድ እየገፋ ነው ሲልም ኮንኗል፡፡

ኦፌኮ በገዥው ፓርቲ ጫና ከምርጫ ውድድሩ መውጣቱን ተናግሮ በኃይል ምርጫን ለማስፈጸም ከመሯሯጥ አስቀድሞ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚመረጥ አሁን አጥብቀን እንመክራለን ሲልም ገልጻል፡፡

አንፃራዊ ሰላም ይታይባታል ከምትባለው ርዕሰ ከተማ ፊንፊኔ/አዲስ አበባን ጨምሮ የመራጮች ምዝገባ ከሚጠበቀው በታች መሆኑ ምርጫው የሕዝቡን ስሜት አለመሳቡን በግልፅ ያመለክታል ነው ያለው ኦፌኮ ፡፡

ይህ የምርጫ ትያቲር ዘመን እንዳለፈም የሚያሳይ ምልክትም ነው ብለን ብሏል፡፡ ሚሊዮኖች የተፈናቀሉበት ዘመን ነው፡፡
ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለን ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል፡፡

ከዕርዳታ ሰጪና አበዳሪ አገሮች ጋር አገራችን እየገባችበት ያለው አለመግባባት ኋላ ላይ ውድ ዋጋ ሊያስከፍላት የሚችል ይመስለናል ብሏል ፓርቲው፡፡

ስለሆነም፤ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ሁሉንም አቀፍ ያልሆነ ምርጫ ከማካሄድ መጣደፉን አቁመው የዕርቅና ብሔራዊ መግባባት መድረክ እንዲያመቻቹና አገራችን ከተጋረጠባት መመሰቃቀል እንዲትወጣ እንዲያደርጉ አበክረን እየጠየቅን፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ኃይሎችና የዓለም ማህበረሰብ ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንድወጣ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንዲታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን ሲል አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *