ኬንያ ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠች፡፡

ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ወደአለባት ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋጧን አሳወቃለች፡፡

ውሳኔው የጭነት በረራዎችን አይመለከትም ተብሏል እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ፡፡
እስካሁን እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንግሊዝ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት ወደ ሕንድ የሚደርጉትን በረራ አቋርጠዋል፡፡

ኬንያ በሚቀጥሉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከሕንድ ወደ ኬንያ የሚመጡ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲገቡ እንደምታደርግም አስታዉቃለች።

ሕንድ ኮሮና ቨይረስ በከፍተኛ ሆኒታ እየጎዳት ያለ ሲሆን ትላንት ብቻ 360ሺህ ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉን ይፋ ሲደረግ ከ3 ሺ በላይ ዜጎቿ ደግሞ በዚሁ ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በሀገሪቱ የሟቹች ቁጥር ከ200 ሺህ መላቁ ተሰምቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *