የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለትንሳኤ በዓል 4ሺህ 5 መቶ የቁም እንስሳትን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ

ድርጅቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ 4 ሺ 5 መቶ የቁም እንሰሳት እርድ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት እንደተደረገ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት አገልግሎት አስተባባሪ አቶ አትክልቲ ገብር ሚካኤል ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንዳሉት በድርጅቱ መሸጫ ሱቆች ለህብረሰተቡ የስጋ አቅርቦትንም ለማድረስ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቁም እንሰሳቱ እርድ እንደሚከናወንም አቶ አትክልቲ አስታዉቀዋል፡፡

እያንዳንዱ የድርጅቱ ሰራተኞች የኮቪድ መከላከያ ህግጋትን እንደሚከተሉ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም እወደ እርድ ቦታዉ የሚንቀሳቀሱ ተሽርካሪዎችም ሆኑ የቁም እንስሳት በኬሚካል የተረጨዉን ቦታ እየረገጡ እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ቀደም ብሎ እርድ የሚካሄድበት ስፍራም ቀደም ብሎ የኬሚካል እርጭት እንደተደረገለት አስተባባሪዉ ነግረዉናል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኮቪድ ወረርሽኝ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ በመምጣቱ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እርዶችን እንዲያከናዉንም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ህገ ወጥ የእርድ አገልግሎት ጤና ፤ለአገር ኢኮኖሚና ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ ችግር ስለሚያስከትል ከዚህ አይነቱ ድርጊት ማህበረሰቡ እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በየአካባቢዉ በጋራ የሚከናወኑ የእርድ ስርዓቶች በመተው ወደ ህጋዊ ቄራዎች ይዞ በመሄድ እንዲያሳርዱ ካልሆነ ግን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንዲያከናዉኑም አሳስበዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሚያዘዝያ 21 ቀን 2013 ዓም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *