በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡

በፋሲካ በአል ቀን ስጋ እየተመገበ የነበረው ወጣት ስጋው አንቆት ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ድንገተኛ የሞት አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካዲስኮ አካባቢ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት የሚዲያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ግለሰቡ ጥሬ ስጋ ገዝቶ በሚበላበት ጊዜ ነው አደጋው የደረሰበት ብለዋል፡፡

ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ሳለ ነው መንገድ ላይ ሂወቱ ሊያፍ የቻለው ብለውናል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜጎች ጥሬ ስጋ በሚመገቡበት አጋጣሚ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሚያዚያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *