የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የብሔራዊ መረጃ ማዕከል ለመገንባት ከአማካሪ ድርጅት ጋር ስምምነት መፈራረሙ ተገለፀ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የብሔራዊ መረጃ ማዕከል ለማስገንባት ከቢዝነስ አፍሪካ ሰርቪስና ኮንሰልታንሲ ኃ.የተ.የግል ማህበርና ከአጋሩ ከያሮን ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት ጋር ሚያዚያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሔደ ስነ-ሥርዓት የውል ስምምነት መፈራረሙን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኤጀንሲው ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኃብታሙ ኃይለሚካኤል እና የቢዝነስ አፍሪካ ሰርቪስና ኮንሰልታንሲ ኃ.የተ.የግ ማህበር ዋና ሥራስኪያጅ አቶ ኪዳኔ ዘሪሁን ናቸውም ተብሏል፡፡

በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የመረጃ ማዕከሉ ተጠሪ የሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በቀጥታ ከኤጀንሲው ጋር እንዲተሳሰሩ በማድረግ ተበታትነው የሚገኙ ስትራቴጂያዊ፣ የኦፕሬሽንና ሌሎች መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አንድ የመረጃ ቋት በማስገባት ለተጠቃሚዎች ግልጽና ተደራሽ ለማድረግና በመረጃ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው የብሔራዊ መረጃ ማዕከሉን ለመገንባት የሚያስችል የገንዘብ እገዛ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ/Agency France Development/ ያገኘ ሲሆን፣ ለውድድር ከቀረቡ 13 ድርጅቶች መካከል ያሸነፈው ቢዝነስ አፍሪካ ሰርቪስና ኮንሰልታንሲ ኃ.የተ.የግል ማህበርና አጋሩ ያሮን ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት ሥራውን በ 8 ሚሊዮን 954 ሺህ 488 ብር ክፍያ እንደሚያከናውንም ጣቢያችን ከኤጀንሲው ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 26 ቀን 2013

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *