ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው በአዲሱ መመሪያ መሰረት ተሽከርካሪዎች የሚቀንሱበት መጠን ይለያያ አንጂ ሁሉም አይነት የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥር ይቀንሳሉ ተብሏል።
የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ታክሲዎች በወንበር ሙሉና እና ከኋላ 3 ሰውና ሃይገሮች (ቅጥቅጦች) በወንበር ልክና ተራርቀው የሚቆሙ 5 ሰዎች ብቻ እንዲጭኑ ታዟል።
ሌሎች የከተማ አውቶቢሶች ደግሞ ከዚህ በፊት ከሚጭኑት ወንበር በ50 በመቶ ቀንሰው እንዲጭኑ በመመሪያው ተገልጿል።
የተሽከርካሪዎች የመጫን አቅም ዝቅ ቢልም በታሪፍ ላይ የተለየ ጭማሪ አይኖርም።
ይህን መመሪያ ተላልፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ከ500 እስከ 5ሺ የሚደርስ ቅጣት እንደሚቀጡ እና የመመሪያውን ተፈጻሚነት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ እንደሚቆጣጠሩት ኃላፊው በመግለጫቸው ተናገረዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም











