በጣሊያን አንድ የፖሊስ መኮንን ገድለዋል የተባሉ ሁለት አሜሪካዊያ የእድሜ ልክ እስራት ተወሰነባቸዉ፡፡

በፈረንጆቹ 2019 በጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ነበር የፖሊስ መኮንኑ የተገደለዉ፡፡

ሁለቱ አሜሪካዊ ወጣቶች ማሪዮ ሴርቼሎ ሬጋ የተባለ ፖሊስ መኮንን ላይ ግድያ የፈጸሙት ምሽት ላይ ለመዝናናት በወጡበት ወቅት በተፈጠረ ድንገተኛ ጸብ በስለታማ ነገሮች በመዉጋት መሆኑን ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

ወጣቶቹ በበኩላቸዉ ድርጊቱን የፈጸሙት ራሳቸዉን ለመከላከል መሆኑን በመግለጽ ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡

ይህን ጉዳይ ለማጣራትም 2 ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ ወስዷል፡፡

በመጨረሻም ወጣቶቹ ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ የእድሜ ልክ እስራት ተወስኖባቸዋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ፕሬስ ቲቪ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሙሉቀን አሰፋ
ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.