የልጃቸዉ ወደ ትምህርት ቤት ሄዶ በሰላም መመለስ ያሳሰባቸዉ እናት 150 ሺህ ዶላር በማዉጣት የአስፓልት መንገድ መሻገሪያ ድልድይ አሰሩ፡፡

በቻይና ሄናን ግዛት የሚኖሩት እኝህ እናት፣ ልጃቸዉ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ አስፓልቱን በደህና ስለመሻገሩ ሁሌም ያስጨንቃቸዉ ነበር፡፡

ትምህርት ቤቱ በዋና መንገድ አቅራቢያ መሆኑ ሳያንስ የትራፊክ መብራት በአካባቢዉ አለመኖሩ የልጆችን ተጋላጭነት በእጅጉ እንደጨመረዉ አንስተዋል፡፡

በዚህም ሁል ጊዜ ስለ ራሳቸዉና ሌሎችም ልጆች ደህንነት አብዝቶ ከመጨነቅ ይልቅ፣ መፍትሄ ያሉትን የመሻገሪያ ድልድይ ወይም ኦቨር ፓስ ብሪጅ፣ 150 ሺህ ዶላር ወይም 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጭ በማድረግ ድልድይ አሰርተዋል፡፡

ሁሉንም ከመንግስትና ከተቋማት መጠበቅ ተገቢ አለመሆኑን ያነሱት እኝህ እናት ይህን ከማድረግ ይልቅ ልጄን ወደሌላ ትምህርት ቤት ወስጄ ባስተምር ይቀለኝ ነበር፤ነገር ግን በዚህ መልኩ ሀገር እና ትዉልድ መገንባት ስለማይቻል ሁላችንም የሚጠበቅብንን ማድረግ ይገባናል፤እኔም ያደረኩት ይህንኑ ነዉ ብለዋል፡፡

ይህ ድርጊታቸዉም ሴትዮዋን እያስወደሳቸዉ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡-ኦዲቲ ሴንትራል

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሙሉቀን አሰፋ
ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.