ሶማሊያ ከኬንያ ጋር ተቋርጦ የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ልታስትካክል እንደሆነ ገልፃለች

ሶማሊያ በታህሳስ ወር ከኬንያ ጋር ያቋረጠችውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደጀመረች አሳውቃለች፡፡

በቅርቡ ከተላለፈው ምርጫ በፊት ሶማሊያ ጎረቤቷ ኬንያን በሀገር ውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ ገብታለች ስትል መክሰሷ የሚታወስ ነው ፡፡

የሁለቱ አገራት ግንኙነቶች ብዙ ጊዜ በውጥረት የተሞሉ ናቸው፡፡

በባህር ውዝግብ ውስጥ ለዓመታት የሰነበቱ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች በነዳጅ የበለፀጉ አካባቢዎችን የይገባኛል ጥያቄ ያነሱባቸዋል እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ፡፡

ኬንያ እስላማዊ ታጣቂ ቡደንን አልሻባብን ለመከላከል በደቡብ ሶማሊያ ወደ 4ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች አሏት፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *