በሽብር ወንጀል የተከሰሰው የሩዋንዳ ጋዜጠኛ በአስር አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በሩዋንዳ የሚገኝ አንድ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ፎካስ ናዳይዜራ እና በስድስት ሌሎች ሰዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ በመመስረት በ 10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

በዋና ከተማዋ ኪጋሊ በሚገኙ የህዝብ ቦታዎች ፍንዳታዎችን በማቀድ እና ሽብርተኝነትን ለመፈፀም በማሴር ጥፋተኛ ተብለው እንደተገኙ ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ዳኛው እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ጥፋቱ ከ 20 እስከ 25 ዓመት የሚያስቀጣ ቢሆንም “ግን እቅዳቸው በመክሽፉ እና በማኅበረሰቡ ላይ ምንም ጎዳት ባለማድርሱ በ10 ዓመት ሊቀጡ ችለዋል ” ብለዋል ፡፡

እንዲሁም ሌሎች ስድስት ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2018 ጋዜጠኛ ፎካስ ናዳይዜራ ፖሊሱዎች ፈንጂዎች ሲሰጡት እና ጥቃቶችን ሲያሴሩ ነበር የተያዙት ፡፡

ይሆን እንጂ ተከሳሹቹ ክሱን ክደዋል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.