በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር በይፋ ከተነገረዉ ከእጥፍ በላይ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሽንግተን ስኩል ኦፍ ሜድሲን የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተዉ፣ 6 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

ጥናቱ እንደሚለዉ ሁሉም ሀገራት በኮቪድ 19 ህይወታቸዉን ያጡ ዜጎችን ትክክለኛ ቁጥር ይፋ አላደረጉም፡፡

አንዳንድ ሀገራት ትክክለኛዉን ቁጥር ባለማወቃቸዉ የመጣ ስህተት ሲሆን አንዳንድ ሃገራት ደግሞ ሆን ብለዉ ቁጥሩን ቀንሰዉ ተናግረዋል ብሏል ጥናቱ፡፡

በጥናቱ መሰረት አሜሪካ 905 ሺህ ዜጎቿን በኮቪድ 19 አጥታለች ያለ ሲሆን በአሜሪካን መንግስት በይፋ ሪፖርት የተደረገዉ ግን 594 ሺህ ብቻ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በደቡብ አሜሪካ፣በካሪቢያን፣ በመካከለኛዉ አዉሮፓና በእስያ ሀገራትም ቫይረሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎችን ህይወት እንደነጠቀ ጥናቱ ጠቅሷል፡፡

የሃገራት ትክክለኛዉን ቁጥር ይፋ አለማድረግ በአጠቃላይ ቫይረሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረሰ ያለዉን ተጽዕኖም በዉል እንዳንረዳ አድርጎናል ብሏል ጥናቱ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ 19 ምክንያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሪፖርት 3 ነጥብ 27 ሚሊዮን አካባቢ መሆኑን የሚያመለክት ቢሆንም፣ ትክክለኛዉ ቁጥር ግን ከ 6 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን ተቋሙ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፡-ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሽንግተን ስኩል ኦፍ ሜድስ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሙሉቀን አሰፋ
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.