በደቡበ ክልል በኮንሶ ዞን በምትገኘው ካራት ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣል፡፡

የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ትናንት ማምሻውን ባውጣው መረጃ እገዳዉ የተጣለዉ በተናጥልም ሆነ በቡድን በመደራጀት የመንግሥትና የግለሰቦች ንብረት የመስረቅና የመዝርፍ ድርጊቶች የእየተበራክቱ በመምጣታቸው መሆኑን ያሳያል።

የከተማዋ የጸጥታ ኃይል ይህንን አጸያፊ መጤ ድርጊት ለመመከት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም እነዚያ ሌቦች፣ ዘራፊዎችና ቀማኞችን በብዙ ጥረት በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድረግ ላይ ቢገኝም ፥ አብዛኛዎቹ እየተሰወሩና በድብቅ እየተደራጁ ጨለማን ተገን በማድረግ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የስርቆት ድርጊቶችን መቀጠላቸውን ይናገራል፡

የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻው ገናሌ እንደሚሉት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማወክ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠልሸት ሌት ተቀን እየሰሩ ያሉ ፀረ ሠላም ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳሉ መንግስት ደርሶባቸዋል፤ ክትትል እያደረገም ይገኛል።

በካራት ከተማ ደረጃ መንግሥት ሁኔታውን በማጤን ለህብረተሰቡ ደህንነት ሲባል ከዚህ በፊት በከተማችን ደረጃ የተወሰነው የጊዜ ሰዓት እላፊ ቁጥጥር ገደብ እንዲበጅለት የካራት ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ባደረጉት ስብሰባ ከውሳኔ ደርሷል ነው ያሉት።

በዚሁ መሠረት:
ባለ ሁለት እና ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማለዳ 12፡00 ሰዓት ማሽከርከር ሲከልከል

መለስተኛና ከባድ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች ምሽት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የጸጥታ አካላት የሚጠይቋቸውን መረጃዎችን የማሳየት ግዴታ እንዳለባቸዉ እንዲሁም ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማለዳ 11፡00 ሰዓት መንቀሳቀስ ሲከለከል ሆቴል፣ ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ መሆኑ ተነግሯል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *