ቻይና የበካይ ጋዝ ልቀት የበለጸጉ ሃገራት በጋራ ከሚለቁት በካይ ጋዝ እንደሚልቅ አዲስ ጥናት አመላክቷል።

ቻይና ወደ ከባቢ አየር የምትለቃቸው ስድስቱ ከፍተኛ ሙቀት አማቂ ጋዞች ማለትም እንደ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ፣ ሜቴን እና ናይትሪዬስ ኦክሳይድ ያሉት ልቀታቸው በ14 ነጥብ 09 ቢሊዮን ቶን ከፍ ብሏል።

ይሄ የቻይና በካይ ጋዝ ልቀት መጨመር ፕሬዝዳንት ዢ ሺንፒንግ ሃገራቸው እስከ 2060 የካርበን ልቀቷን ወደ ዜሮ ለመቀነስ ትሰራለች ያሉትን ሃሳብ አጠናክረው እንዲይዙ የሚያሳስብ ሆኗል።

ዛሬ ላይ ቻይና ብቻዋን 27 ከመቶ የአለማችንን ከባቢ አየር በካይ ጋዞች የምትለቅ ሲሆን አሜሪካ በ11 ከመቶ ትከታላለች።

ህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ 6.6 ከመቶ የበካይ ጋዝ ልቀት በማስመዝገብ የአውሮፓ ህብረት አባላትን በልጣ ተገኝታለች።

አለማችንን በህዝብ ብዛት የምትመራው ቻይና ከሌሎች የበለጸጉ ሃገራት አንጻር ስትታይ ለከባቢ አየር በካይ ጋዞችን መልቀቅ የጀመረችው በቅርቡ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከነዚህ ሃገራት የላቀ በካይ ጋዝ በመልቀቅ የቀዳሚነቱን ስፍራ መያዝ ችላለች ይላል አልጀዚራ በዘገባው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጄ
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *