በህንድ ሰሜናዊ ክፍል በጋንጀስ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሰዎች አስክሬን ተገኘ፡፡

በሰሜናዊ ህንድ በጋንጀስ ወንዝ ዳርቻ ቢያንስ የ 40 ሰዎች አስክሬን በውሃ ተገፍቶ መገኘቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

አስከሬኖቹ እንዴት እንደመጡ ግልፅ ባይሆንም የአካባቢው የመገናኛ ብዙሃን የኮቪድ-19 ሰለባዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል፡፡

አስክሬኖቹ በቢሃር እና በኡታር ፕራዴሽ ግዛቶች ድንበር አቅራቢያ መገኘታቸውን በተመለከተ ቢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እስከ 100 የሚደርሱ አስክሬኖች መገኘታቸውን ዘግበዋል፡፡ አስከሬኖቹ በወንዙ ውስጥ ለብዙ ቀናት እንደቆዩ ጠቅሰዋል ፡፡

አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት “አስክሬኖቹ ከኡታር ፕራዴሽ የመምጣት ዕድል አላቸው” ብለዋል፡፡

ኡታር ፕራዴሽ በሕንድ ውስጥ በጣም ብዙ የህዝብ ቁጥር ያለው ክልል ነው፡፡

ሁለተኛው የኮቪድ ማዕበል ሕንድን ያጥለቀለቃት ሲሆን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በቫይረሱ ህይወታቸው የሚያልፉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

አብዛኛዎቹ የአገሪቱ የሬሳ ማቃጠያ ስፍራዎችም ሞልተዋል ይላል የአልጀዚራ ዘገባ፡፡

አገሪቱ አሁን የዓለም ዋነኛ ወረርሽኝ ማዕከል ሆናለች፡፡

ሕንድ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከ 22.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ሲያዙ 246 ሺህ 116 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሙያዎቹ ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል እያሉ ይገኛሉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *