በእየሩሳሌም የተነሳው አመጽ እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ አለምአቀፍ ልመናዎች እየተሰሙ ነው፡፡

በእስራኤላውያን እና ፍልስጥኤማውያን መካከል የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት እንዲረግብም አሜሪካ፣ አውሮፓ ሕብረት እና እንግሊዝ ሁለቱ ወገኖች ችግሮችን ከማባባስ እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለውጥረቱ መነሻ የሆነው በምስራቅ እየሩሳሌም በሚገኘው የሼክ ጃራ ክፍል የፍልስጤማዊያን ለማፈናቀል ታሰቧል መባሉን ተከትሉሎ ነው እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው እስካሁን በዚህ አመጽ 21 ፍሊስጤማዊያን ህይታቸው ማለፉን ከፍልስጤም ጤና ሚኒስትር ሰማሁ ብሉ ዘግቧል፡፡

ከሟቾቹ መካከልም ህጻናት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ከ300 የሚበልጡ ፍልስጤማዊያን ሰልፈኞችን ጨምሮ ከ 20 በላይ የእስራኤል ፖሊሶች ባለፈው ሶስት ቀናት በነበሩ ግጭቶች ተጎድተዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊው አንቶኒ ብሊንከን ሀማስ የሮኬት ተኩሱን በፍጥነት እንዲቆምና ሁለቱም ወገኖች ነገሮችን ለማበብረድ ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ፕሬዝደን ጆ ባይደን እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ እንዳሳሰባቸውና ግጭቱ በፍጥነት እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይዋ ጄን ሳክ አስታውቀዋል።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ዶሚኒክ ራብ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ”በሮኬት የሚፈጸሙት ጥቃቶች መቆም አለባቸው፤ የንጹሀን ዜጎች ኢላማ መሆንም መቆም አለበት” ብለዋል።

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬልም በበኩላቸው ”በዌስትባንክ፣ ጋዛ እና ምስራቃዊ እየሩሳሌም እየጨመረ የመጣው ግጭት በፍጥነት መቆም አለበት” ብለዋል።

ሰኞ ዕለት በቅዱሱ የእየሩሳሌም አካባቢ ከእስራኤል ፖሊሶች ጋር በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን መጎዳታቸውን ተከትሎ ሃማስ የአጸፋ ምላሽ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደግሞ ሀማስ ‘ቀዩን መስመር ተላልፏል’ እስራኤልም ብትሆን ለሚደርሰው ነገር በሙሉ በከፍተኛ ኃይል ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት በበኩሉ ትናንት ሰኞ ዕለት በጉዳዩ ላይ አስቸጓይ ስብሰባ አካሂዷል።

ነገር ግን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መግለጫ አላወጣም።

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.