በጋምቤላ ክልል በሁለት ጎሳዎች መካከል የሚፈጠረውን ግጭት ለማስቆም እየተሰራ መሆኑ ተነገረ፡፡

በክልሉ በኑዌር ዞን በሚገኙ የቻንቻይ እና የቻንጎዎ ጎሳዎች መካከል በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እንደሚፈጠሩ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በዞኑ በተለያዩ ጊዜያት በድንበርና በሌሎችም ምክንያቶች በሚፈጠር ግጭትም የሰዎች ህይወት እያለፈና ንብረትም እየወደመ ይገኛል፡፡

በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ባለፈው ዓመት በተፈጠረ ግጭት የ 12 ያክል ሰዎች ህይወት ማለፉን ያስታወሱት ሃላፊው በዞኑ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ያለው ቂም በቀል እያገረሸ በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እንዲፈጠሩ እያደረገ እንደሚገኝ ሃላፊው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሁለት ጎሳዎች በደቡብ ሱዳንም እንደሚገኙ የነገሩን አቶ ኦቶው በዞኑ ግጭት ሲከሰት ከደቡብ ሱዳን በመምጣት ለሚወክሏቸው ጎሳዎች ወግኖ የማጥቃት ልማድ መኖሩንም ነው ያነሱልን፡፡

ይህንን የጎሳ ቅራኔ ለመፍታትም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንደተሰባሰቡና ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝም እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎችና አባቶች በዚህ ላይ ከፍተኛ ሚና እያደረጉ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡

በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በምትኘው ኔዌር ዞን በሁለቱ ጎሳዎች በተፈጠረ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኢትዮ ኤፍ ኤም መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *