ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል በመላ ሀገሪቱ ያለው የክልልና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል ከሌሎች የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር ኮሚሽኑ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ነው አስታወቋል፡፡

«ኢስላም» እና «ሰላም» የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው የተነሳ መላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ይህ ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.