በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል የተጠረጠረውን አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ነው።

በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላለፏል፡፡

“ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ ብሏል፡፡

ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ኮሚሽኑ ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ ስለ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል ‘የአባ ቶርቤ’ ቡድን አባል በመሆኑ ‘እርምጃ ተወስዶበታል’ በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በበኩሉ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና ‘የአባ ቶርቤ’ ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል።

የከተማው ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይም ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አትሟል።

በአካባቢው በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የ”ሸኔ” ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.