በ1.5 ቢሊየን ብር የተገነባው ዘመናዊ ማተሚያ ቤት በቅርቡ ይመረቃል

በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በ1.5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ ማተሚያ ቤት በቅርቡ እንደሚመረቅ ተነግሯል፡፡

ከ5 አመት በፊት የተጀመረው የግንባታው ሂደት ተጠናቅቆ የህትመት መሳሪያዎች መገጠማቸውን ና በቅርቡም እንደሚመረቅ የማተሚያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ቃሲም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

95 በመቶ በመንግስትና 5 በመቶ በባንኮች ባለቤትነት የተገነባው ማተሚያ ቤቱ የማሽኖቹ ግዢ ሂደት በአራት ጊዜ የጨረታ ሂደት የተሳካ መሆኑንም አቶ መሀመድ ጨምረው ነግረውናል፡፡

ዘመናዊው ማተሚያ ቤት ከሚስጥራዊ ህትመቶች በስተቀር ሌሎችን ህትመቶች እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡

የማተሚያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወደፊት ሚስጥራዊ ህትመቱንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማውራት ልንጀምር እንችላለን ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጄ
ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *