እስራኤል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች፡፡

በእስራኤል ሃይሎችና በዓረብ እስራዔላዊያን መካከል ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው አዋጁ መታወጁን ቢቢቢ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡

ሰሞኑን የፍሊስጤም ሃይሎች በእስራኤል ማእከላዊ ከተማዎች ላይ በሮኬት የታገዙ ጥቃቶችን ሲያደርሱ መሰንበታቸውን መረጃው አስታውቋል፡፡

እስራኤልም በአጸፋው በፍሊስጤም የጋዛ ሰርጥ ላይ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት ህንጻወችን ከማውደሟም ባለፈ፤ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የቢቢሲ መረጃ አስታውሷል፡፡

የእስራኤል ጥቃት ያነጣጠረው በፍሊስጤም ጋዛ ውስጥ የሚገኙ ተፋላሚ ሃይሎች ላይ ሲሆን የፍሊስጤም ሃይሎች ደግሞ የእስራኤልን ከተማ ቴላአቪቭ መሆኑን መረጃው አመላክቷል፡፡

ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ በፍሊስጤም ታጣቂ ሃይሎች ወደ እስራኤል ማእከላዊ ከተማዎች ከ1 ሺህ የሚበልጡ ሮኬቶች መተኮሳቸውን እንዲሁም እስራኤል ደግሞ 200 ሚሳኤሎችን መተኮሷ ተነግሯል፡፡

በፍሊስጤም የጋዛ ሃይሎችና በሀገሪቷ ሃይሎች መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ፤ በዚህም የንጹኃን ዜጎች ሞት እየጨመረ በመሆኑ እስራኤል ሎድ በተባለችዋ ከተማና ሌሎች ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸዉ አካባቢዎች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.