1.3 ሚሊዮን እናቶች አሁንም ድረስ ከህክምና ተቋማት ውጪ እንደሚወልዱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በየአመቱ ነፍሰ ጡር ከሚሆኑ እናቶች 3.2 ሚሊዮን መካከል 1.3 ሚሊዮን ያህሉ በቤታቸው እንደሚወልዱ ተሰማ

ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው እናቶች በቤታቸው መውለዳቸው ደግሞ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እየሰራን ነው ለሚለው ጤና ሚኒስቴር አዳጋች ሆኖብናል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር ዶክተር መሰረት ዘላለም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም በምትለው ኢትዮጵያም፣ በአመት 11ሺ በላይ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡም የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

የጤና ኤክስቴንሽ ባለሙያዎች ህብረተሰቡን በማስተማር እና ወደ ጤና ተቋማት እንዲሄድ የተወጡት ሚና ከፍተኛ ቢሆንም አሁንም የበለጠ የማህበረሰብ ንቅናቄ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የወሊድ መቆጣጥሪያ አጠቃቀምን በተመለከተም መድረስ ያለብን ደረጃ ባንደርስም መሻሻል ግን እንዳለ ዶክተር መሰረት ተናግረዋል።

ሀገራችን የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚመዘገብባቸው ሀገራት ተርታ ትሰለፋለች።

የእናቶችን እና የህጻናትን ሞት ቁጥርም ለመቀነስ ጤና ሚኒስቴር ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ እንደሚሰራም ዶክተር መሰረት ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
መቅደላዊት ደረጄ
ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *