ከሱዳን በመነሳት በማይካድራ አድርጎ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ 320 የህወሃት ታጣቂ ሀይል ተደመሰሰ፡፡

የህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደተናገሩት

በማይካድራ ጭፍጨፋ አድርሶ ወደ ሱዳን በመሸሽ ተደራጅቶ የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችንና መድሀኒቶችን በመያዝ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሙከራ ያደረገው የህወሃት የጥፋት ሀይል ተደምስሷል ብለዋል።

ሀላፊው በሰጡት መግለጫ ፣ ሀገራዊ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በአሜሪካ ይገኙ የነበሩና ሀገርን በመካድ ሱዳን ካርቱም ከሚገኙ የጁንታው አመራሮች ጋር ወደ ሀገር ውስጥ የመገናኛ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ በሰራዊታችን ተደምስሰዋል ብለዋል።

በሱዳን መንገድ ላይ በውሀ ጥም የተንጠባጠቡ አባላቶቹና እጃቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆኑትም ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብለዋል።

ብዛት ያለው የሬድዮ መገናኛ ፣ ሳተላይት ስልኮችና መድሀኒትም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

ምንጭ፡-የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *