የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት አስር ወራት ለውጭ ገብያ ከቀረቡ የተለያዩ ማዕድናት 6 ሺህ 785 ነጥብ 42ኪሎ ግራም ማዕድን ለውጭ ገቢያ ቀርቦ 513 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብሏል።
ይህም ለውጭ ገብያ ለማቅረብ ከታቀደው 5 ሺህ 921 ነጥብ 52 ኪ.ግ የማዕድን ምርት እንዲሁም ከሚላከው ምርት ለማግኘት ከታቀደው 501.73 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ብልጫ እንዳለዉ አስታዉቋል።
ይህ ገቢ የተገኘው ከባህላዊ ማዕድን አምራቾች ጀምሮ መካከለኛ እና ከፍተኛ የማዕድን አምራች ኢንዲስትሪዎች ድረስ አበርክቷቸው የጎላ መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስተር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአስገኘው ገቢ ባሻገር የሀብት ብክነት ባሳዩ የማዕድን ልማት ላይ ለመስራት ፍቃድ የወሰዱ ከዚህ ቀደም 63 ተቋማት ፍቃዳቸው የተሰረዘ ሲሆን በድጋሚ በተደረገ ማጣራት 27 የማዕድን አውጪ ተቋማት ከዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ፍቃዳቸው ተሰርዟል፤ እንዲሁም ለ3 የማዕድን አውጪ ተቋማት ስህተታቸውን አርመው ወደ ስራ እንዲገቡ በአፋጣኝ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጨምረው ገልጸዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም











