የኮሮና ቫይረስን በመመርመር በ 30 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚያሳውቅ ዘመናዊ የመመርመሪያ ማሽን ወደ ሃገር ውስጥ መግባቱን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ 19 ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር መብራቱ ማሴቦ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
እንደዚህ ዓይነቱን ተግባር ለመከወን ወደ ሃገር ውስጥ የገቡት ዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎችም ቁጥራቸው 8 መቶ ሺ እንደሚደርሱ ሰምተናል፡፡
24 ሚሊዮን ብር ወጪ የወጣባቸው እነዚህ ዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎች በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ ዶ/ር መብራቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡
ላለፉት ወራት ሃገሪቱ በቀን የምታካሂደው የኮሮና ቫይረስ የናሙና ምርመራ እጅግ በጣም ዝቅ እያለ መምጣቱን ተከትሎ እንደ ሃገር የመመርመር አቅማችንን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከሚደረገውና ከ 5 ሺ ያልዘለለውን የናሙና ምርመራ አቅምን በማሳደግ በቀጣይ በቀን 14 ሺ ያክል ናሙና መወሰድ የሚያስችለን ደረጃ ላይ ለመገኘት እየሰራን ስለመሆኑም ነግረውናል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 09 ቀን 2013 ዓ.ም











