የህዳሴዉ ግድብ ሁለተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌት ግብጽን እንደማይጎዳ የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድጋሚ አረጋገጡ

የግብፅ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ ኢትዮጵያ ሁለተኛዉን ዙር የህዳሴ ግድብ የዉሃ ሙሌት ብታካሂድ በአገራቸዉ ላይ ጉዳት እንዳማያደርስ መናገራቸዉን ኢጂፕት ኢንዴፔንደንት ዘግቧል፡፡

ከዚህ ቀድም ሁለተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌቱ ምንም አይነት ጉዳት አያደርስብንም ያሉት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሁንም በድጋሚ ይህንኑ ሃሳባቸዉን ደግመዉታል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት ያነሱት የአስዋን ግድብ በቂ ዉሃ ክምችት ስለያዘ ኢትዮጵያ ግድቧን ብትሞላ የሚያስከትለዉ ጉዳት የለም ነዉ ያሉት፡፡

አሁን ላይ በሙሉ መተማመን የህዳሴ ግድቡ ሙሌት በእኛ ላይ ጉዳት አያደርስም ሲሉ የተናገሩት ሹኩሪ ነገር ግን አሁንም በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ዉይይቶችን እና ድርድሩን እንቀጥላለን ማለታቸዉን ዘገባዉ አስፍሯል፡፡

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሶስቱ አገራት ድርድር በአፍሪካ ህብረት እንዲካሄድ ፍላጎት ማሳየቱም ለጉዳዩ እየሰጡት ያለዉን ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ የሶስትዮሽ ድርድርሩ በአፍሪካ ህብረት እንዲካሄድ ከመጀመሪዉ ጀምሮ ፅኑ አቋም የነበራት ሲሆን ግብፅና ሱዳን ግን ጉዳዩን ወደተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና አገራት ለመዉሰድ ሲሞክሩ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ካይሮና ካርቱም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቋማቸዉን ሲለዋወጡ መመልከት አዲስ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በመጪዉ የክረምት ወቅት ሁለተኛዉን ዙር የዉሃ ሙሌት የምታካሂድ ሲሆን አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱም ታዉቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *