ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለት ቀናት ውስጥ ሊፈርም ይችላል ተባለ

አንድ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን በቀን ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ የጋዛ ታጣቂዎችና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈርሙ ይችሉ ብለዋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት “ለእስራኤል ዜጎች ሰላምና ደኅንነት እስኪመለስ ድረስ ጥቃቱን እንቀጥልበታለን” ብለዋል።

ትላንት ከሰአት በኃላ ብቻ ከመቶ በላይ የእስራኤል የአየር ጥቃቶች በሐማስ ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ተተኩሰዋል፡፡

የፍልስጤም ታጣቂዎች የአጸፋ ምላሽ ሰተዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡

የጋዛው ግጭት የተጀመረው በእስራኤልና ፍልስጤማዊያኑ መሀል እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢ በረመዳን ወር ለቀናት ውጥረት ከነገሠ በኋላ ነው።

ሙስሊሞችና አይሁዳዊያን ቅዱስ ቦታችን ነው በሚሉት አል አቅሳ የደማስቆ በር መግቢያ ላይ የእስራኤል ወታደሮች ክልከላ በማድረጋቸው ጋዛን የሚቆጣጠረው ሐማስ ቁጣውን ሲገልጽ ቆይቷል።

እስካሁን በጋዛ ከ 100 በላይ ሴቶችንና ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 227 ሰዎች መገደላቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አስታውቋል፡፡

በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150ዎቹ ታጣቂዎች መሆናቸውን እስራኤል አስታውቃለች፡፡

ሀማስ እስካሁን በእርሱ ወገን ስለተጎዱት ተዋጊዎች ቁጥር ምንም አላለም ፡፡

በእስራኤል ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ 12 ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

በጋዛ በሚገኙ ታጣቂዎች ወደ 4000 ያህል ሮኬቶች ወደ ግዛቷ እንደተተኮሱ እስራኤል ገልጻለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.