የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን 528 ቤቶች በዕጣ ሊያስረክብ እንደሆነ ተነገረ፡፡

የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት እና ሰራዊቱን የቤት ባለቤት ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመው የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሜ/ጀ ኩምሳ ሻንቆ አንዳስታወቁት በአሁኑ ሰዓት 3ሺ12 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ 528 ቤቶች ደግሞ በዚህ አመት ለዕጣ ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

በቃሊቲ ቁጥር 1 ሳይት 584 ቤቶች ፣ ቃሊቲ ቁጥር ሁለት 504 ቤቶች በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ 1ሺ88 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ ፣ ግንባታቸው 56 በመቶ ደርሷል፡፡

በሚቀጥለው አመት ተጠናቀው ለሰራዊታችን አገልግሎት ይሰጣሉ ብለዋል።

በቢሾፍቱ አካባቢ 2 መቶ ባለ 1 እና ባለ 2 መኝታ ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ ብሏል፡፡

አፈጻጸማቸው 76 በመቶ በመድረሱ በአሁኑ አመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዳማ ሳይት ፣ 2 ብሎክ 80 ቤቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውንና አፈጻጸሙ 73 በመቶ በመድረሱ በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በመቐለ ሳይት ፣ 11 ብሎክ 440 ቤቶች ከ1 እስከ 3 መኝታ ቤቶች ግንባታ ላይ መሆኑን ገልጸው ፣ ሽብርተኛው ጁንታና ተላላኪዎቹ በፈጠሩት ፀጥታ ችግር ምክንያት የግንባታ ስራው ተጓቷል የማቴሪያል ዝርፊያና አንድ ተሸከርካሪም ተወስዷል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት ፋውንዴሽኑ ግንባታው 60 በመቶ የደረሰውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚጠናቀቅ ሜ/ጀ ኩምሳ ሻንቆ ተናግረዋል።

በባህርዳር ሣይት በ2012 ዓ/ም 312 ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ ቤቶች ተጀምረው በአሁኑ ሰኣት 52 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በሀዋሳ ሳይት አራት ኮንትራክተሮች መኖራቸውን ገልጸው ፣ 320 ቤቶች በግንባታ ላይ መሆኑንና 95 በመቶ መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሜ/ጀ ኩምሳ ሻንቆ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *