ዲያዝ የእግር ኳስ ጸሃፍት ማህበር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል

የ24 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ ተከላካይ የፖርቱጋሉን ቤንፊካ ለቅቆ በ65 ሚ.ፓ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለው ባለፈው ክረምት ነበር፡፡

ማንቸስተር ሲቲ የፕሪምየር ሊጉን እና የካራባኦ ዋንጫን እንዲያሸንፍ በእጅጉ አግዟል፡፡

ለቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ለመድረሱም አስተዋጽኦው የጎላ ነበር፡፡

‹‹ትልቅ ክብር ነው፡፡ ቡድኔ ስኬታማ ባይሆን ይህንን ሽልማት ላገኝ እንደማልችል ግልጽ ነው፡፡ እኔ የዚህ ሽልማት አሸናፊ መሆኔ ቡድናችን ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ያሳያል›› ብሏል ዲያዝ ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአቤል ጀቤሳ
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *