ግብፅ በሁለት ሳምንት ውስጥ 35 ዶክተሮችን በኮሮና ቫይረስ አጣታለች

የሀገሪቱ የህክምና ህብረት ባወጣው መረጃ መሰረት ግብፅ በሁለት ሳምንት ውስጥ
35 ዶክተሮችን አጣታለች።

ማህበሩ እንዳለው እስካሁን 500 ሀኪሞች ሞተዋል።

በግብፅ ከሚሞቱት ጠቅላላ ሰዎች ብዛት ውስጥ የዶክተሮች ጥምርታ ከአሜሪካ ጋር ሲነፃፀር ስድስት እጥፍ ይበልጣል ፡፡

በግብፅ በኮሮና ቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በትክክል ከተዘገበው እጅግ ከፍ ያለ እንደሚሆን በሰፊው ተዘግቧል እንደ ሚዲል ኢስት ሙኒተር ዘግባ፡፡

ጉዳዮን ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሪፖርት በማድረጋቸው ሀኪሞችና ሌሎች የህክምና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አንዳንዶቹም ለእስር ተዳርገዋል ፡፡

የግብፅ የዶክተሮች ህብረት ባለስልጣናት ቤተሰቦቻቸው በቂ የገንዘብ ካሳ እንዲያገኙ ትክክለኛውን ቁጥር እንዲነገር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.