6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ለሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት በሆቴል ዲሊኦፖል እየተሰጠ በሚገኘው መግለጫ ላይ የቦርዱ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሶሊያና ሽመልስ እንዳሉት ምርጫዉ ሰኔ 14 ቀን 2013 እንዲካሄድ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት ምርጫዉ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሰኞ እለት ይካሄዳል ነዉ የተባለዉ፡፡

የመራጮች ምዝገባ ላይ ቅሬታ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ግን ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድም ምርጫ ቦርድ አስታዉቋል፡፡

ቀደም ሲል የ6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 በሚል ቀን ተቆርጦለት እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡

በዳዊት አስታጥቄ

ግንቦት 12 ቀን፣ 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.