የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለግብር ከፋዮች ምህረት በማድረጉ 10 ቢሊየን ብር ማጣቱን ተነግሯል፡፡

ላለፉት 11 ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ግብራቸውን ሳይከፍሉ የቀሩ በንግድ ሥራ ላይ የነበሩ የከተማው ነዋሪዎች ከስራ ከሚወጡ በሚል የተላለፈ ውሳኔ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዋና ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ምህረት የተደረገላቸው 7 ሺ ለሚደርሱ ከ1997-2007 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ግብር ክፍያ እዳ ላለባቸው ነጋዴዎች ነው፡፡

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ሊያገኝ ይገባ የነበረውን 10ቢሊየን ብር ማጣቱን ገልጸው ምህረት የተደረገላቸውን የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ወደ ስራ ተመልሰው የተሻለ ገቢ የሚያስገቡበት መንገድ እንዲሰሩ እና የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንዲሰሩ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

ገቢዎች ቢሮ በሰራቸው የግንዛቤ ስራዎች የተሻሻለ የግብር ከፋይ ቁጥር ቢኖርም አሁንም ግን ይቀራል ተብሏል፡፡

በዚህም በ2013 ዓ.ም 10 ወር ብቻ 250 የሚሆኑ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ባለመፈጸማቸው እርምጃ መወሰዱንም ሰምተናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጄ
ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.