በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሣሪያ ተግባራዊ ተደርጓል የሚለውን የተሳሳተ ክስ እንደማትቀበለው ኢትዮጵያ አስታወቀች

የኢትዮጵያ መንግስት በህግ ማስከበር ዘመቻው በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያን ሳይጠቀም አልቀረም በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቋል ።

በተለይም ዘ ቴሌግራፍ በተሰኘው ጋዜጣ ላይ ዊል ብሮውን የተባለ በናይሮቢ የጋዜጣው ወኪል በዛሬው ዕለት በወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያን ተጠቅማ በርካታ ዜጎች ተጎጂ ሆነዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ክፉኛ ተችቷል ።

በህግ ማስከበር ዘመቻው ኢትዮጵያ ይህ አይነቱን የጦር መሳሪያ በፍፁም አልተጠቀመችም ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ፣ አገሪቱ የአለም አቀፍን ህግ የምታከብርና በማንናቸውም እና በየትኛውም ቦታ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተግባራዊ ሲደረግም ድርጊቱን የምትኮንን ነች ብሏል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈበርከውን አሳሳች መሠረተ ቢስ አሉባልታ እንዲያቆምም መግለጫው አስጠንቅቋል።

ምክንያቱም ይህ አይነቱ አሉባልታና ጫና ተጨማሪ ቀውስ ሊያስከትል ስለሚችል የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.