አሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ባለስልጣነት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ማሰቧን አስታወቀች

አገሪቱ በትግራይ ክልል ያለዉ አለመረጋጋት እንደሚያሳስባት በመግለፅ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ እንደምታደርግ አስታዉቃለች፡፡

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቲዉተር ሰሌዳቸዉ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትግራይ ክልል ያለዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በተደጋጋሚ ድምጻችንን ብናሰማም ችግሩ ባለመቆሙ ከዛሬ ጀምሮ እገዳዉን እናስተላልፋለን ነዉ ያሉት፡፡

ዋሽንግተን እገዳዉ የሚጣልባቸዉን ግለሰቦች ስም ባትጠቅስም ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉ ባለስልጣናት እንደሚሆኑ ብሊንከን ይፋ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ባደረገችዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምእራባዉያን በአገር ዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ነዉ በሚል ስትቃወም መቆየቷ ይታወሳል፡፡

በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንም በዉስጥ ጉዳያችን ላይ ጣልቃ አትግቡ፤ ሉኣላዊነታችን ይከበርልን የሚል መልዕክቶችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እያሰሙ ቢገኙም አሜሪካ ግን አሁንም ጣልቃ መግባቷን ቀጥላለች፡፡

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.