ኢትዮጵያ የአሜሪካ ዉሳኔ ከጉዞዋ ወደ ኋላ እንደማያስቀራት አስታወቀች

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ እንደሚጥል ማስተላፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣዉ መግለጫ ኢትዮጵያና አሜሪካ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸዉ አገራት ሆነዉ ሳለ አሜሪካ በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ አሳዛኝና ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ሲል ወቅሷል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ያስተላለፈዉ ዉሳኔ የኢትዮጵያን ጉዞ እንደማያሰናክል የገለፀዉ መግለጫዉ ይልቁንም ኢትዮጵያ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረምር ና አማራጮችን እንድታስብ ትገደዳለች ነዉ ያለዉ ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በዉሳኔዉ ሳይገደብ በዉስጥም ከዉጭም የሚሰነዘሩ ጫናዎችን መታገሉን እንደሚቀጥልም በመግለጫዉ አንስቷል፡፡

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ አናዳጅ ብቻም ሳይሆን ዘመናትን ያስቆጠረዉን የሁለቱን አገራት ግንኙት የሚጎዳ ነዉ ሲል ክፉኛ ነቅፏል፡፡

ኢትዮጵያ የአገር ዉስጥ ችግሮቿን እንዴት መፍታት እንዳለባት ማንም ሊነግራት አይችልም ያለዉ መግለጫዉ የአሜሪካ መንግስት በኢትጵያ የዉስጥ ጉዳይ ለመግባት እያደረገ ያለዉ ሙከራ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ብሏል፡፡

በትግራይ ያለዉ አለመረጋጋትና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከማንም በላይ የኢትዮጵያን መንግስት ያሳስበዋል ያለዉ የዉጭ ጉዳይ መግለጫ ችግሩንም ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብሏል፡፡

አሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ባለስልጣነት ላይ የጉዞ እገዳ እንደምትጥል ማሳወቋ የሚታወስ ሲሆን አገሪቱ በትግራይ ክልል ያለዉ አለመረጋጋት እንደሚያሳስባት በመግለፅ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ እንደምታደርግ ገልፃች፡፡

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቲዉተር ሰሌዳቸዉ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትግራይ ክልል ያለዉ የሰብኣዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በተደጋጋሚ ድምጻችንን ብናሰማም ችግሩ ባለመቆሙ ከዛሬ ጀምሮ እገዳዉን እናስተላልፋለን ነዉ ያሉት፡፡

ዋሽንግተን እገዳዉ የሚጣልባቸዉን ግለሰቦች ስም ባይጠቅስም ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉ ባለስልጣናት እንደሚሆኑ ብሊንከን ይፋ አድርገዉ ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *