የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያና ሱዳን ከማሸማገል ገለል ማለቷ ተሰማ

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር ጉዳይ ለገቡበት ውዝግብ የጋራ መፍትሄ ስታፈላልግ የቆየችው የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውዝግቡን በራሳቸው ይፍቱት ማለቷ ተሰምቷል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም የዉዝግቡ ምንጭ በሆነዉ የአል-ፋሽቃ አካባቢ የግብርና ፕሮጀክቶችን ልታለማ ነዉ በሚልም ስሟ ተደጋግሞ ተጠቅሶ ነበር፡፡

በአቡዳቢ የሚታተመዉን “አሻርክ” የተባለን ጋዜጣ ዋቢ አድርጎ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበዉ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሁለቱ ሀገራት የገቡበትን ዉዝግብ በራሳቸዉ እንዲፈቱ ለሱዳን ቁርጡን ነግራታለች ብሏል፡፡

ችግሩንም በሰላማዊ መንገድ መፍታት ላይ እንዲያተኩሩ ነዉ ሀገሪቷ የገለጸችዉ፡፡

የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1902፣ 1903 እና 1972 የተፈረሙ ስምምነቶችን ለማደስ እንደፈለገች በማስመሰል ስሟን እየጠቀሱ ከፍ ሲልም እያጠለሹ መሆኑንም ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

የሱዳን የገንዘብ ሚንስትር ጅብሪል ኢብራሂም የገልፍ ሃገራት በአካባቢዉ የ 8 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶችን ለማልማት መጠየቃቸዉን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የድንበር ጉዳያችሁን በራሳችሁ ጨርሱ ስትል ለሱዳን አሳዉቃለች ተብሏል ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሙሉቀን አሰፋ
ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *