ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተነገረ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባሳለፍነው ሳምንት 1ሺህ 1 መቶ 36 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሣምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ በተከናወነው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዜጎችን ወደ አገራቸው መመለስ ተችሏል ነው ያሉት።

ዜጎቹ በተለያዩ አገራት በተለይም በሳውዲ እና በሌሎችም የአረብ አገራት በችግር ላይ የነበሩ እንደሆነም ተነስቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቃል አቀባዩ በመግለጫው የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

በተለይም የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት ያላገናዘበ እንደሆነ አንስተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ጉዳይ በተለይም በትግራይ ባለው ሁኔታ ላይ የተዛባ መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ ነዉ ያሉት፡፡

ከአባይ ወንዝ እና ከተፋሰሱ አገራት ግንኙነት ጋር በተያያዘ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትበብር ማዕቀፍ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል ።

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *