አወስትራሊያ በአፍጋኒስታን ያላትን ኤምባሲ ልተዘጋ ነዉ፡፡

በማዕከላዊ እስያ የምትገኘው አፍጋኒስታን ከፍተኛ የሰላም ቀውስ ውስጥ መሆኗን ተከትሎ፣አውስትራሊያ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማዋ ካቡል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንደምተዘጋው በጠቅላይ ሚኒስቴሯ ስኮት ሞሪሰን እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ማሪስ ፔይን በኩል ያስታወቀችዉ፡፡

አውስትራሊያ ይህን ውሳኔ ለመወሰን በአሪቱ ያለው አለመረጋት እና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ አለመሆኑ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት የአውስትራሊያ ዲፕሎማቶች ለጉብኝት ወደ አፍጋኒስታን ገብተው እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን፣ ነገር ግን በዋና ከተማዋ በ‹‹ካቡል›› ግን ደፍረው አልተንቀሳቀሱም ነው የተባለው፡፡

ያለውን የሰላም ቀውስ ምክንያት አድርገውም በሚያዚያ ወር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ አፍጋኒስታን ስትልክ ከሃያ አመታ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ተሳተፍን በማለት ተናግረው ነበር፡፡

በዚህም አውስትራሊያ እንዳለችዉ በቀጣይ አርብ በዋና ከተማዋ ያለውን ኤምባሲ እንደምትዘጋና ግዜያዊ ጽ/ ቤት እንደምትከፍት አስታዉቃለች፡፡

ከዛም ባለፈ አውስትራሊያ ከአፍጋኒስታን ጋር ጠንካራ ግንኙነቷን እንደምትቀጥል እና ሀገሪቱ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንድትመለስ ድጋፏ እንደማይለያትም አረጋግጣለች፡፡

ካቡል በውስጧል 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ይኖርባታል፡፡

ቢቢሲ

በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *