በጉራፈርዳ ታጣቂዎች ጥቃት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በጠቅላላው180 ያህል ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፍርዳ ወራዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የአካባቢው እና የፌደራል የጸጥታ አባላት ጨምሮ 180 ያህል ዜጎች ህይወታቸው አጥተዋል ተባለ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከንጹሀን ዜጎች በተጨማሪም 28 የፀጥታ አካላት የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን ከ29 በላይ ደግሞ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

21 ሺህ 938 የአከባቢው ነዋሪዎች ጥቃት ሊሰነዘርብን ይችላል በማለት ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንዲሁም በጉራፈርዳ እና በደቡብ ቤንች ወረዳዎች ከ732 በላይ የቆርቆሮና የሳር ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተነግሯል፡፡

በአካባቢው የንግድ እንቅስቃሴ ፣የእርሻና ሌሎችም ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው እንዲሁም የህብረተሰቡ ማህበራዊ መስተጋብርም ችግር ውስጥ መውደቁን ነው የተነገረው፡፡

ለህብረተሰቡ ስጋት የሆኑት ታጣቂዎች በየጫካና በህብረተሰቡ መካከል ሆነው የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር እየተጠቀሙ አሁንም በፀጥታ ሀይሉና በንፁሀን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ እየፈጸሙ እንደሚገኙ ነው የተነገረው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *