ብሊንከን አሜሪካ ከፍልስጤማውያን ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታድስ ቃል ገቡ፡፡

አሜሪካ በኢየሩሳሌም ቆንስላ በመክፈት ከፍልስጤማውያን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ቃል የገባች ሲሆን ይህም በግጭቱ የተጎሳቆለውን የጋዛ ሰርጥ መልሶ ለመገንባት እንደሚረዳ ዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል ገብቷል ፡፡

ብሊንከን በትናንትናው ዕለት ከፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በራመላህ ባደረጉት ውይይት አሜሪካ ከፍልስጤማውያን ጋር ያላትን በሚኖራት አጋርነት ዙሪያ በጥልቀት መወያየታቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ፍልስጤማውያን የአሜሪካን ቆንስላ በኢየሩሳሌም የመክፈት ሂደትን ለማራመድም ቃል ገብተዋል፡፡

ቆንስላው በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ. በ 2019 የተዘጋ ሲሆን በወቅቱ ፍልስጤማውያንን ያስቆጣ እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ያበላሸ ነበር፡፡

ጋዛን መልሶ ለመገንባት ለመርዳት የባይደን አስተዳደር በቅርቡ 75 ሚሊዮን ዶላር (£ 52m) ድጋፍ ለማግኘት ኮንግረሱን እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ ለጋዛ በአፋጣኝ የ 5.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እና 32 ሚሊዮን ዶላር ለተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ድርጅትና እና ለፍልስጤም ስደተኞች እንደምትሰጥ አክለዋል፡፡

የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.