አርሶ አደሩ በጥራት ያዘጋጀውን ቡና በጥሩ ዋጋ ለመሸጥ የሚስችለው አዲስ የግብይት አሰራር ይፋ መደረጉና ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የቡና ግብይት ስርዓት (Micro Lot Coffee Trading Platform) የተሰኘ አሰራር ይፋ ተደርጓል፡፡

ዶ/ር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እና አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው የግብይት ፕላት ፎርሙ ይፋ የተደረገው፡፡

በምርት ገበያ መሪነት የሚዘጋጀው ይህ ሁነት አርሶ አደሮቹ በአካል ቀርበው የቡና ምርታቸውን ለውድድር የሚያቀርቡበት እንደሆነ የኢትዮጲያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በየወሩ የሚደረገው ይህ የግብይት ስርዓት፤ አሸናፊው በጨረታ ተመርጦ የሚታወቅበት በመሆኑ ለገበያ የሚቀርበውን የቡና ጥራት ከመጨመር ባሻገር ፣ አዲስ ጣዕም ያላቸውን ቡና ምርት ለመለየት ፣ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡

የገበያ ውድድሩንም ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑንም ባሻገር በቡና ስራ ለፍተው፣ ደክመው፣ ጥረው እየተጎሳቆሉም ቢሆን በቡና ላይ ተስፋ ባለመቁረጥ ቡናቸውን ለማቆየት የሚፍጨረጨሩትን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በመንግስት ኩል በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ አሰራር ለሽያጭ የሚቀርቡ ቡናዎችም ዋጋቸው እጅግ አማላይ የሆነና አርሶ አደሩንም ሆነ አቅራቢውን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችለው አሰራር ነው ተብሏል፡፡

አሰራሩ በተለይም የጥራት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ቡናዎችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪ እንድንሆን እና በዋጋ የመደራደር አቅማችንንም በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር የአገራችንን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍ የማድረግ ሚና እንደሚኖረው እና አርሶ አደሩንም ተጠቃሚ በማድረግ ገቢውን ከማሳደግ በተጨማሪ በርካታና አዳዲስ የውጭ ቡና ገዢ ድርጅቶችንም ትኩረት እንደሚስብ ተናግረዋል፡፡

ከፍላጎት አንጻር ከፍተኛ ፍላጎት ያለው የቡና ምርት ጥራትን አኳያ ባደረገ መንገድ አቅርቦት ላይ ዝቅተኛ መሆኑ ቀደም ሲል ይስተዋል ነበር፡፡

ባለፈው አስር ወራት የኢትዮጲያ ምርት ገበያ ካገበያያቸው ምርቶች አንዱ ቡና ሲሆን በ10 ወራት ውስጥ ለተጠቃሚ 201ሺህ401 ቶን ቡና ቀርቦ በ21.8 ቢሊየን ብር መገብየቱን የሚታወስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *