ኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችን ገዝቶ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው የህይወት አድንና መሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት አፈጻጸም 81% የመሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት ደግሞ 65% እንደነበር ገልፃል፡፡

ኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም የህይወት አድንና መሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት 81% የመሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት ደግሞ 65% እንደነበር ከ13 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችን እንዳሠራጨ ተገልፃል፡፡

ኤጀንሲው የጤና ተቋማትን ፍላጎት ለማሟላት ባሣለፍነው 9 ወራት 11 ቢሊየን 173 ሚሊየን 412 ሺህ 78 ብር የሚያወጡ የመደበኛና የፕሮግራም መድኃኒቶችን ገዝቶ ማቅረቡን የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተናግረዋል፡፡

በኤጀንሲው ግዥ በመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ከነበረውና በበጀት ዓመቱ ግዥ ከፈፀመው መድኃኒት 14 ቢሊየን 259 ሚሊየን 360 ሺህ 471 ብር መድኃኒቶችን ለማሰራጨት አቅዶ 13 ቢሊየን 4 ሚሊየን 680 ሺ 689.04 ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች መሰራጨታቸው ተገልጿል።

ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን የጤና ተቋማትን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ስላላሟለን፣ አቅርቦት አና ፍላጎት እስከሚጣጣም ድረስ ጠንክረን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

የኮቪድ 19 በሽታን ለመግታትና ለመቆጣጠር 1 ቢሊዮን 743 ሚሊዮን 754 ሺህ 302 ብር ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን በማሰራጨት ኤጀንሲው ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን ኤጀንሲው በማህራዊ የትስስር ገፁ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
የውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *