የአሜሪካው ሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ የባይደን አስተዳደር በኢትዪጵያ መንግስት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ::

የኦክላሃማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ የአሜሪካ መንግስት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን የቪዛ ማዕቀብ ከባድ እጅ (Heavy handed) ሲሉ በቱዊተር ገፃቸው ላይ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል::

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳዎችን እቃወማለሁ፣ ኢትዮጵያ ሁከት እና ግጭትን ለማስቆም እየሰራች ባለችበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የእኛን ድጋፍ እገዛ እንጅ እገዳ አያሻትም ብለዋል፡፡

እንደ ቪዛ እቀባ ያሉ እርምጃዎችም ወደ ሰላማዊ መፍትሄ እንድንቀርብ አይረዱንም በማለት አንጋፋው ሴናተር በኢትዮጵያ ላይ የተጣለው እገዳ ፍፁም ለኢትዮጵያ የማይረዳ እና አሜሪካም ሰላም አመጣለሁ የምትለውን የማያሳካ መሆኑን በግልፅ ተቃውመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.