የኮሮና ቫይረስ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ተባለ

የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ከአንድ አመት ወዲህ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ሲጋራ ማጨስ እንዳቆሙ የኢትዮጵያ የምግብና የመድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳሬክተር ወ/ት ሄራን ገርባ ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን ምን ያህል ዜጎች ሲጋራ ማጨስ እንዳቆሙ ቁጥራዊ መረጃዎች ባይኖርም በመላው አለም የአጫሾች ቁጥር ግን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ከ15 አመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች ወጣቶች ጎልማሶች የትምባሆ ምርት መጠቀምን በሚመለከት በተካሄደው ሀገራዊ ጥናት መሰረት 29.3 ከመቶ ወይም 6.5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ለደባል አጫሽነት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

በተለይ እንደ ሆቴል፣ ሬስቶራንት፣ መዝናኛ ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች እና መሰል ቦታዎች የሚሰሩ እና የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለደባል አጫሽነት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖከ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *