ደቡብ ሱዳን ‘በምንም መንገድ ከኢትዮጲያ ጥቅም በተቃራኒ የሚሠሩ ኃይሎችን አትታገስም’ የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ

የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል ሳንቲኖ ዴንግ ዎል ሀገራቸው ኢትዮጵያን ለመጉዳት ሲሰሩ ከሚታዩ ሀገሮች ወይም ግለሰቦች ጋር እንደማትተባበር ለኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ይህንን ያለችው የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እና የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ ሳንቲኖ ደንግ በጁባ ምክክር ባደረጎበት ወቅት ነው።

አምባሳደሩ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ሥራ እና ቀጣይ የሰብአዊ ድጋፎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል መደበኛውን እንቅስቃሴ ለመመለስ የሚያደርገውን ስራ ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ እና በመጪው ምርጫ ላይ መግለጫ ሰተዋል እንደ ሱዳን ፖስት ዘገባ፡፡

የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ በበኩላቸው “በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ጥሩ ግንኙነት እና ትብብር” በማስታወስ “ኢትዮጵያ ለአገራቸው ያበረከተችው አስተዋጽኦ የማይረሳ ነው” ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.