በፔሩ በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል

ፔሩ ያላት 33 ሚሊየን ህዝብ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 1 መቶ 80 ሺ ዜጎቿን ማጣቷ ተነግሯል፡፡

በፔሩ በኮቪድ-19 የሟቾችን ቁጥር ከእጥፍ በላይ እየሆነ መምጣቱንም የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ አመላክቷል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፔሩ በቅርቡ የሟቾች ቁጥር 69 ሺህ 342 የነበረ ቢሆንም ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ ሳቢያ በአሁኑ ሰዓት ከ 180 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ለሞቱ ችለዋል፡፡

ፔሩ በላቲን አሜሪካ ካሉ እጅግ በጣም በቫይረሱ ከተጎዱ ሃገሮች አንዷ ስትሆን ያልዘመነ የጤና አጠባበቅ ስርዓቷ እና የኦክስጂን እጥረት መከሰት እንዲሁም የክትባት ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆን ለወረሽኙ መስፋፋት ምቹ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.